ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት የሚደርስባቸውን ጫና ለማስቀረት ትልቅ አቅም ይፈጥራል

ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት የሚደርስባቸውን ጫና ለማስቀረት ትልቅ አቅም ይፈጥራል”

በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት በዓለም ለ114ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ “ማብቃትና መብት ማስጠበቅ ለሁሉም ሤቶች እና ወጣቶች” በሚል መሪ ቃል ሁሉም የተቋሙ ሴት አመራሮች እና ፈፃሚዎች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አምባዬ ወልዴም ሴቶች ላይ የሚደርሡ ጥቃቶች እና ጫናዎች ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት ከሚደረጉ ጥረቶች ጎን ለጎግ ቀጣዩን ትውልድ በስነምግባር በማነፅ እና በፆታ እኩልነት ግንዛቤ አዳብረው እንዲያድጉ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለሴቶች ድጋፍ ማድረግ ቤተሰብን ብሎም ሃገርን መደገፍ ነው ያሉት ሃላፊው በኮሚሽኑም ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ብሎም ጠንካራ አመራሮች ሆነው እንዲወጡ ከማስቻል አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቃል ገብተዋል፡፡

ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ከሚደርስባቸው ጫና ለመታደግ ሚናው የጎላ ነው ያሉት ደግሞ በኮሚሽኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሃመልማል ክብሬ ሢሆኑ በኢኮኖሚ የበቁ ሴቶች ከጥገኝነት በመላቀቅና በራሳቸው የመወሰን አቅማቸውን በማጎልበት ከሚደርስባቸው ጫና እና ተፅእኖ እራሳቸውን ለመከላከል አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡

ሃላፊዋ አክለውም በአሁኑ ወቅት በኅብረት ሥራ ቁጠባ እና ብድር ዘርፍ ከተቆጠበው ከ57 ቢሊዮን በላይ ብር ውስጥ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 46 በመቶው የተቆጠበው በሴቶች መሆኑ እና የብድር አመላለስ እና በኦዲት ሪፖርት የተሻለ አፈፃፀም እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ ይህም ሴቶች በውስን ድጋፍ ትልቅ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ማሳያ ነው ብለዋል ሃላፊዋ፡፡

በበዓል አከባበሩ በስርዓተ ፆታ፣ በማህጸን እና ጡት ካንሰር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ በተጨማሪም የተቋሙን ብሎም በኅብረት ሥራ የተደራጁ እንስቶችን ማብቃት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

+2

All reactions:

1111

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top