ወጋገን ባንክ ከአማራ ክልል ኀብረት ስራ ማበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን “ሜንዞ ፋይናሻል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሶልሽን” በሚል የትግበራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
ግንቦት 19/2017 ዓ.ም(ኀ/ስ/ማ/ማ/ባ) በሙከራ ደረጃ የሲስተም ልማት ትግበራው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኘው በደሴ አምባ የኀብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን እና በአንድ አባል መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበራት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ሙከራው ውጤታማ ከሆነ ወደ ሌሎች የሚሰፋ እንደሆን በመግባባቢያ ስምምነቱ ላይ ተገልፃል፡፡
ወጋገን ባንኩ በሃገሪቱ ካሉት ከኀብረት ስራ ማህበራት ጋር በትብብር የመስራት የካበተ ልምዱን ተጠቅሞ አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን እና ሌሎችንም ፋይናሻል ስራዎችን ሊያሰራ የሚችል ዲጅታላዜሽን እንደሆነ የተገለፀው በተለይም ኢንተርኔት በሌለበት ቦታ ሁሉ አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነም ተገልፃል፡፡
ወደ ትግበራ ሲገባ በኀብረት ስራ ማህበራት የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን ለመፍታት ፣የጥሬ ገንዘብ እጥረቶችን ለመፍታት እና ዘመናዊ አሰራርን እንዲከተሉ እንደሚያስችልም ተገልፃል፡፡
ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለውን የአባላት ፍላጎት በአግባቡ መመለስ የሚያስችል ነው፡፡
አገልግሎቶችን በማንኛውም ቦታና በፈለጉት ሰዓት እንዲያገኙ ለመርዳትና አባላት በኤሌክትሮኒክ ክፍያ ዘዴዎች ገንዘባቸውን ማዘዋወር የሚያስችል ነው። ይህም የፋይናንስ ዘርፉ በዲጂታል አማራጮች ተጠቅሞ ዝውውሩ እንዲፈፀም ከፍተኛውን ድርሻ እንዳለው ተገልፃል፡፡ፓኬጁ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ተጠናቆ እርክክብ የሚፈፀምና ወደ ተግባር እንደሚገባም ተገልፃል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የአብክመ ኀብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን እና ወጋገን ባንክ ተፈራርመዋል፡፡
