ለኢንቨስትመንት አማራጮች መዳረሻ በሆነችው ጓንጓ ወረዳ በ2.4 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው ግዙፍ መጋዝን የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ተከናወነ።
ታህሳስ 01/2017 ዓ.ም (ኀ/ስ/ማ/ማባ))
በአዊ ብሔ/አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ ሉንስ ደገራ ቀበሌ በአድማስ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒዬን የሚገነባው ግዙፍ መጋዝን የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ፕሮግራም ተከናውኗል።
ወረዳው ለኢንቨስትመንት ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በርካታ አልሚ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍ ጥያቄዎችን እያቀረቡ እንደሚገኝ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ቦጋለ ጠቅሰዋል።
አያይዘውም የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ለወጣቶች የሚፈጥረው የስራ ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት እና በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ወረዳው አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
ግንባታውን በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የጠቀሱት የዩኒየኑ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፉዬ አዲስ ሲሆኑ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ120 ሺህ ኩንታል በላይ መያዝ እንደሚችል ገልፀዋል።



