በአማራ ክልል አዊ ዞን የሚገኘው ዉራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን በ22/03/2017 ዓ.ም አጋርና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚገም ቅርንጫፍ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

በአማራ ክልል አዊ ዞን የሚገኘው ዉራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን በ22/03/2017 ዓ.ም አጋርና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚገም ቅርንጫፍ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

ዚገም በ22/2017 ውራ ዩኒየን # የዩኒየኑ የ2016 በጀት አመት እቅድ ክንውን አፈፃፀም እና የዘመኑና የውዝፍ ብድር አመላለስ የነበሩ ጥንካሬዎችና እጥረቶች በተመለከተ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷልቀ።በንቅናቄ መድረኩም የዚገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ የኔው፣የወረዳው ፍትህ ሀላፊዎች፣ፖሊስ ሀላፊዎች፣ሠላምና ደህንነት ሀላፊዎች ፣የብልፅግ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣የወረዳው የህብረት ስራ ማህበራት መስፋፊያ ፅ/ቤት የማኔጅመንት አባላት፣ የውራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ፣የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ አመራር አካላት፣የግብርና ሀላፊዎች፣በዚገም ወረዳ ስር ያሉ የቀበሌ የመንግስት መዋቅር አመራሮች የዚገም ቅርንጫፍ የውራ ዩኒየን አባል ማህበራት አመራሮች በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አድርጓል። በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው መድረኩን የከፈቱት፣የአጠቃለሉትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የሰጡት የዚገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ አለነ ሲሆኑ ህብረት ስራ ማህበራት ለወረዳው፡፣ለብሔ/አስ፣ ለክልሉ ብሎም ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት የድርሻቸውን ሚና እየተወጡ ያሉ ተቋማት ናቸው ብለዋል።አክለውም ህዝባችን የቁጠባ ባህል በማሳደግ፣በማዳበርና አባላት የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑና በተናጠል መፍታት የማይችሉትን ችግሮቻቸውን በጋራ እንዲፈቱ ያደረጉና እያደረጉ ያሉ ተቋማት በመሆናቸው ልደግፋቸው ይገባል ያሉት ሀላፊው በመሆኑም የተበደርነውን ብድር በወቅቱ መመለስ ግዴታ ነው ብለዋል።

# የንቅናቄ ሰነድ ያቀረቡት የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሴ ምናየው ዩኒየኑ እስከ ህዳር 22/03/2017ድረስ * 121 መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራትን አባላት ያደረገ መሆኑ፣* ካፒታል ግንባታ 68;900;000ብር የፈጠረ፣* ሀብት 388;300;000ብር ያለው፣* ትርፍ ክፍፍል ለአባላት በ2016 በጀት 17;900;000ብር ማከፋፈሉ የቻለ፣.*ብድር ለአባላት እስከ ህዳር 22/2017 ድረስ 328;000;000ብር እንደሰጠ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

# በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪዎ አቶ መልካም አለነ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ተግባራት ዙሪያ የስራ አቅጣጫ ሰጠዋል።

1. የወረዳና የቀበሌ አመራሩ ብድር ማስመለስና ከብድር ነፃ የሆነ ቀበሌ ለመፍጠር በኢንሸቲቭ እቅድ ተካቶ እንደወረዳ እየሰራን ስለሆነ ይህን ለመፈፀም ለማስፈፀም ከራሡ ጀምሮ የርብርብ አካል ማድረግ፣

2. የመሠረታዊ የገ/ቁ/ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ስራ አመራር አካላት እስከ ታህሳስ 10/2017 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ የተበደሩትን ውዝፍ ብድር እንዲመልሱ፣

3. እስከ ታህሳስ 30/2017 ዓ/ም ድረስ ሌሎች አባላት የተበደሩትን ውዝፍ ብድር ሙሉ በሙሉ እንዲመልሱ፣

4. የብድር አመላለስ ሂደቱን በቼክ ሊስት መሰረት መዋቅራዊ ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ በየሳምንቱ በጥቅል አመራር እየተገመገመ መመራት፣የወረዳ አመራሩ በየተመደበበት ቀበሌ በየቀኑ የውዝፍ ብድር አመላላስ ያለበትን ሁኔታ ለወረዳው ኮር አመራር መረጃ መለዋዎጥና በመቀናጀት ውጤታማ ስራ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top