የአዊ ብሔ/አስ/ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ መምሪያ 3ኛ ዙር ሥልጠና በስሩ ላሉ የወረዳ ባለሙያዎችና ቡድን መሪዎች ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
እንጅባራ ህዳር 24/2017 የአዊ ብሔ/አስተዳድር ህብረት ስራ ማስፋፊያ መምሪያ 3ዙር በስሩ ላሉ የወረዳ ፅ/ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የመ/ማህበራት ቅጥር ሰራተኞችና ስራ አመራር አካላት በተገኙበት ስልጠና መስጠት ጀመረ። በገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራት ተግባራት አፈፃፀም ወቅት የነበሩ ችግሮች ፣የመሠረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀት መመሪያ፣ በሒሳብ አያያዝ ፣ የንግድ ስራ ዕቅድ አዘገጃጀት እና የገንዘብ ቁጠባ ብድር የህብረት ስራ ማህበራት የማጠናከር እስትራቴጅ/ሞዴል ፈጠራ/ አሰራሮችና መመሪያዎች በተመለከተ 3ኛ ዙር ስልጠና መስጠት ጀምሯል።በስልጠናውም፦ የወረዳ ፅ/ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ቡድን መሪዎች፣ባለሙያዎች፣ሞዴል የተመረጡ የ12 መሠረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራት ቅጥር ሠራተኞችና የስራ አመራር አባላት እየተሳተፉ መሆኑን
ከወጣው መርሃ_ግብር መረዳት ተችሏል።
# በሥልጠና ፕሮግራሙ ተገኝተው የሥልጠና መክቻ ያደረጉት የአዊ ብሔ/አስ/ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ዳኘው ሲሆኑ፦ስልጠናው ያስፈለገበት ምክኒያት ተቀራራቢ የሆነ አቅም በባለሙያው መካከል ለመገንባት፣የሚታዩ የአፈፃፀም ጉድለቶችን ለመሙላት፣የሀብት አስተዳድር አሠራርን የተሟላ አድርጎ ለመፈፀም፣ሞዴል ሜህበራትን ለመፍጠርና ወደ ሌሎች ለማስፋት እና የህብረት ስራ ማህበራትን በማጠናከር የአባላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስልጠናው አስፈልጓል ብለው።በስልጠናው መሳካት ያለባቸው ነጥቦች *የሰልጣኙን አቅም መገንባት፣በስልጠና ወቅት የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን መሙላት፣የህብረት ስራ ማህበራትን አሠራር፣አደረጃጀቶችንና መመሪያዎችን ማጠናከር የሚታዩ ጉድለቶችን መሙላት፣የህብረት ስራ ማህበራትን ደህንነታቸውን ማስጠበቅ ትኩረት የሚደረጉባቸው አላማዎች እንዲሳኩ መደረግ አለበት ብለዋል።በስተመጨረሻውም ሠልጣኞች በአምስት ቀን ቆይታቸው የሥልጠናውን አላማ በወል ተገንዝበው እርስ በእርሳቸው ልምድ በመለዋዎጥ ያላቸውን ክፍተት በመሙላት ለቀጣይ ስራ መዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።



