ገነቷ የተፈጥሮ ሀብት ህብረት ስራ ማህበር ሙሉ ኢኮቱሪዝም መንደር ጮቄ – ሙሉ ኢኮ ሎጅ
ደጋ ዳሞት – ጎጃም
ሁሌም አረንጓዴ ምድር ነው። ቦታው በጣም ቀዝቃዛና ረግረጋማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጮቄ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በአማካኝ 4100 ሜትር ከፍታ ያለው ጮቄ በተለምዶ የጎጃም ጣራ በመባል ይጠራል፡፡
የጮቄ ተራራ ሰፊ ተፋሰስ የሚሸፍን ሲሆን ሰባት የሚሆኑ የምስራቅ ጎጃምና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎችን ያዋስናል። ከነዚህ ወረዳዎች መካከል በምዕራብ ጎጃም የሚገኘው የደጋ ዳሞት ወረዳ አንዱ ነው።
ደጋ ዳሞት እ.ኤ.አ በ2022 የዓለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር (Best Tourism Village) አሸናፊ የሆነው የሙሉ ኢኮ ሎጅ መገኛ ነው። በገነት የተፈጥሮ ሀብት ቱሪዝም ህብረት ሥራ ማህበር የሚተዳደረው ሙሉ ኢኮ ሎጅ ማህበረሰብ ተኮር ቱሪዝምን በማስፋፋት እና አካባቢን በመጠበቅ በመጀመሪያው የድንቅ ምድር የእውቅናና ሽልማት መረሃ-ግብርም አሸናፊ የሆነ ድንቅ ሎጅ ነው።





