ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዛሬን በኀብረት ሥራ እናልማ !

ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዛሬን በኀብረት ሥራ እናልማ !

********

የኀብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የኀብረት ሥራ ማህበራት ዕድገትና ተወዳዳሪነት ማሻሻያ ሪፎርም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ለመሆኑ በሃገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ልማት እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ከኀብረት ሥራ ማህበራት ምን ይጠበቃል?

• የአባላት ገቢን በማሻሻል የኑሮ ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ፣ በገጠርና ከተማ የሥራ ዕድል በመፍጠር ድህነትና ሥራ አጥነትን በመቀነስ እና በገጠርና ከተማ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት በማሳደግ ኢንቨስትመንት በማስፋፋት ያላቸውን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጊዜውን የጠበቀና አቅምን ያገናዘበ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና ግብዓቶች ለአርሶና አርብቶ አደሩ በማቅረብ፣ ሥልጠና በመስጠት፣ መሰረተ ልማትና አገልግሎቶች እንዲያገኙ በማድረግ አምራቾች የምርት ፍላጎትና የጥራት ደረጃን አሟልተው በተሻለ ደረጃ ምርት እንዲያቀርቡ በማስቻል የሃገር ውስጥና የውጪ ገበያ ተደራሽነታቸውን እናንዲያሳድጉ የላቀ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• አባላት ሥልጠናና ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ በሀብት አያያዝና አጠቃቀም ክህሎታቸውን እንዲገነቡ ማስቻል፣ የህዝብ ለህዝብ መቀራረብና የእርስ በራስ መረዳዳት እንዲጎለብት በማድረግ ያላቸውን ሚና በላቀ ደረጃ ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

• የአካባቢ ዘላቂ ደህንነትን በመጠበቅ፣ ከብክለት የጸዳ ታዳሽ ሀይል በመጠቀም፣ የአካባቢ መራቆትና ብክለትን የማያስከትል ምርት በማምረት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመቋቋም የላቀ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• የሴቶችና ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ያላቸውን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

• በአጠቃላይ በምግብ ዋስትና፣ በድህነት ቅነሳና በገጠር ልማት መንግስት ለሚተገብራቸው አዳዲስ የልማት ውጥኖች አመርቂ ተሳትፎ በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማሳካት ከኅብረት ሥራ ማህበራት ይጠበቃል፡፡

ስለሆነም ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዛሬን በኀብረት ሥራ እናልማ !

የአትዮጱያ ኀብረት ስራ ኮሚሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top