የደቡብ ወሎ ዞን የመስክ ስምሪት ቡድን አባላት በዛሬው እለት ማለትም ከታዩ ማህበራት እና ወረዳ አንፃር የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ ውይይት ዞኑ ላይ የዞኑን ማኔጅሜንት አባላትና ኃላፊ በመያዝ በጥንካሬ እና በድክመት የስምሪት ቡድኑ በአካል ያደረገውን ድጋፍ እንዲሁም ማኔጅመንቱ የሰጠውንም የሪፎርም ግብረመልስ መሰረት ያደረገ ውይይት አድርጓል በውይይቱም በእጥረት የተነሱ በተለይም ከሪፎርም ተግባራችን ወደስራ ያልገቡ ማህበራትን ከማፍረስና ደካማ ህብረት ስራ ማህበራትን ከማዋሃድ አንፃር በቀጣይ በትኩረት ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተሰጧል። ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ህብረት ስራ ማህበራትን ወደ ተሻለ የግብይት አፈፃፀም ከማስገባት አንፃር የተስተዋሉ ጉለቶችን በጥንካሬ ለመፈፀም የሚያስችል አቅጣጫን በማስቀመጥ ውይይቱ ከተካሄደ በኋላ የዞኑን የግብርና መምሪያ ኃላፊ የሆኑትን አቶ አህመድ ጋሎን በውይይት በተነሱ ሃሳብችና በጋራ ተግባራችን ዙሪያ በማወያየት ተጠናቋል።
