በቀን 11/03/2017 ዓ.ም
ወደ ምስራቅ አማራ የተጓዘው የኀብረት ስራ ማህበራ ማስፋፊያ ባለስልጣን የክትትልና ድጋፍ ለማድረግ የሄደው ቡድን ስራዎቻችን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት የተቀመጡ ግቦችን በየጊዜው እየገመገሙና ማስተካከያ በማድረግ በልዩ ትኩረት መፈፀም እንዲቻል በበጀት ዓመቱ እስከ አሁን ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት ማዕከል በማድረግ በመስክ ድጋፉ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸውን ዋና ዋና ተግባራትን መሰረት ያደረግ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ፡፡
ደሴ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ የገንዘብና ቁጠባ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር በአካል በመገኘት የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የሪፎርም ተግባራቸው አፈፃፀም ያለበትን ደረጃና በተግባር ያጋጠሙ እጥረቶችን በለየመልኩ ከማህበሩ ሊቀመንበር ና የቅጥር ሰራተኞችን በተገኙበት ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ውይይት ተደርጓል ። ማህበሩን ሊያሳድጉ የሚችሉ እየተከኒወኑ ያሉ ተግባራትን ለማየት ጥረት ተደርጓል።ከዚህም ጋር ተያይዞ የማህበሩ አመሠራረት የቅርብ የሚባል ቢሆንም አቅዶ እየተንቀሳቀሰበት ያለውን አበረታች ሁኔታዎችን ለማየት ችሏል።
