የእፅዋት ዘር ጥራት ማስጠበቅ፣ቁጥጥርና ማረጋገጥ ዙሪያ በዘር ብዜት ለተሰማሩ ለኀብረት ስራ ማህበራት ስልጠና እየተሰጠ ነው
ባህር ዳር ፤ህዳር 13/2017 ዓ.ም (ኀ/ስ/ማ/ማ/ባ)
የክልሉን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዕጥረት የሚቀርፍና የግብርና ምርት ዕድገትን በማሳደግ ረገድ ሚናው የጎላ እና ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የግብርና ልማት ለማረጋገጥ የማያቋርጥ የቴክኖሎጅ አቅርቦት መኖር የዘር ብዜት ግብይት ኅብረት ሥራ ማህበራት እንደ ሌሎች የግብርና ግብዓቶች የተለያዩ ምርጥ ዘሮችንም በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋና በወቅቱ እንዲቀርብ ለማድረግ በደቡብ ጎንደር፣ሰሜን ጎጃም ፣ምዕራብ ጎጃም ለሚገኙ የዘር ብዜት ግብይት ኀብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒዬኖች ቅጥር ሰራተኞች፣የዞን ባለሙያዎች በተገኙበት ስልጠና እየተሰጠ ይገናል፡፡
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አጀበ ስኒሻው እንደገለፁት የዘር ብዜት ኅብረት ሥራ ማህበራት ትክክለኛ የሆነ መስራች ዘር በሚፈለገው መጠን፣ጊዜና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙና እንዲጠቀሙ ማድረግ የድህነትን ቅነሣ ግብ በማሣካት ረገድ ትርጉም ያለው ድርሻ ያለው እንደሆነ በክልሉ የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘሮችን በማባዛት ከሚሳተፉ ተዋንያን መካከል በዘር ማምረትና ግብይት የተሰማሩ ኅብረት ሥራ ማህበራት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የገለፁት፡፡
በየደረጃው በሚደረገው ጥረትና ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አባላት የማኅበራቸውን እንቅስቃሴ በቅርበት በመከታተል፣ አባላት ሲጠቀሙ እኔም እጠቀማለሁ የሚለውን በማረጋገጥ በመኽር የተመረተውን ዘር በተገቢው በጥራት የማሰባሰብ፣ ከተሰበሰበ በኃላ ወደ ማከማቻ በተገቢው የማከማቸትና የማስበጠር ስራ በመስራት የማጓጓዝ ተግባራት በትኩረት መሰራት እንዳለበት የገለፁሲሆን ለዚህ ደግሞ የመጋዝን መሰረተልማትና ፋይናንስ በተገቢው መዘጋጀት እንዳለበት ገልፃዋል፡፡
ስልጠናው በዘር ማሰባሰብ ፣ማከማቸትናአያያዝ እንዲሁም ማጓጓዝ እና የግዥና ሽያጭ ላይ ትኩረት ተሰጦ ስልጠናው ይካሄዳል ፡፡
