የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት  በኀብረት ስራ ማህበራት  እየተሰራ  መሆኑን የኀብረት ስራ ኮሚሽን   አስታወቀ፡፡

ህዳር 11/2018 ዓ.ም (ኀ/ስራ ኮሚሽን) የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት በኀብረት ስራ ማህበራት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን   የኮሚሽኑ የግብዓትና ግብይት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ አለምዘውድ ስሜኔህ     የገለፁ ሲሆን  ኅብረት ሥራ ማኅበራት በራሳቸው ካፒታልና ከተማ አሰተዳደርና ወረዳዎቹ ባመቻቹት ተዘዋዋሪ ፈንድ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በበጀት አመቱ ባለፉት  ወራት እየቀረበ መሆኑን ገለፁ፡፡

አቶ አለምዘውድ ስሜነህ   እንደገለፁት በክልሉ በ22 ዞንና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ኅብረት ስራ ማህበራት ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ለገበያ ማረጋጊያ አላማ የሚውል  955 ሚሊየን 665 ሺህ 600 ብር እንዲሰጣቸው ተጠይቆ 910 ሚሊየን 957 ሺህ 658  ብር በላይ  የተፈቀደለቀቸው ሲሆን  በተለቀቀላቸው  ገንዘብ  እና  የራሳቸውን ካፒታል በመጨመር  የተለያዩ የግብርናና የፋብሪካ ምርቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ገበያ በማረጋጋት  በክልል የሚገኙ የሸማቾች ኀብረት ስራ ማኅበራት እና  ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ስራ ማህበራት የግብርና ምርቶችና የኢንድስትሪ ምርቶችን  በማቅረብ ተሳትፈዋል፡፡

በበጀት አመቱ ባለፉት ወራት የግብርና ምርት 62,301  ኩንታል፤ 1 ቢሊየን 137 ሚሊየን 757 ሺህ 245 ብር የሚያወጣ የኢንዱስትሪ ምርቶች ምርት የዳቦ ዱቄት  ፤ ምግብ ዘይት  ፤ ስኳር እና ሌሎችን የእንስሳት ውጤቶችን ጨምሮ  ከገበያ ባነሰ ዋጋ ለአባላትና አባል ላልሆኑ  ለመንግስት ሰራተኞችና ለዝቅተኛ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በማሰራጨት የኑሮ ውድነቱ በሸማቹ ላይ አላስፈላጊ ጫና እንዳያደርስ ማድረግ ተችሏል  ሲሉ  አቶ አለምዘውድ  ገልፀዋል፡፡

አያያዘውም  በከተሞች   የመንግስት ሰራተኞችን  ያቀፈ   የሸማቾች ኀብረት ስራ ማህበራት  በማቋቋም ገበያን ለማረጋጋት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንደተቻለም ገልጸዋል።አሁን ላይ የኑሮ ውድነትን ለማስታገስ እየቀረበ ያለው የግብርና የኢንዱስትሪ  ምርት ጅምር ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል ።

የሸማቾች ኀብረት ስራ ማህበራት እና ሌሎች ኀብረት ስራ ማህበራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና  የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትን የማዋሃድ፣ የማደራጀት፣ የማፍረስ፣ አዳዲስ አባላትን የማፍራት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው በየደረጃው የሚገኙ የሸማቾች እና ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ስራ ማህበራት  ገበያን በማረጋጋት በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም  አቶ አለምዘውድ  እንዳሉት መንግስት በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በዞኑ ለሚገኙ  የገጠር ወረዳዎችና እና ከተማ አስተዳደር ለሚገኙት  ተዘዋዋሪ ገንዘብ በመመደብ  የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top